Jump to content

ተረትና ምሰሌ

ከWikiquote
  • የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ
  • የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
  • የነፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
  • ከአህያ የዋለች ፈረስ ፈስ ተምራ ትገባለች
  • ጉልቻ ቢቀያያር ወጥ አያጣፍጥም
  • ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት
  • አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሃፍ አጠበች
  • ኑሮ ካሉት መቃብርም ይሞቃል
  • ኣንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል።
  • ኣይጥ ሞቷን ስትሻ የድመት ኣፍንጫ ታሸታለች።
  • ላም ያልዋለበት ኩበት ለቀማ።
  • ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ።
  • ዥብ ከሄደ ውሻ ጮኸ።
  • ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል።